| | መዝ 50:9-10 እኔ ግን ኮርማህን ከበረት፣ ፍየሎችህንም ከጒረኖ የምፈልግ አይደለሁም፤ የዱር አራዊት ሁሉ፣ በሺ ተራራዎች ላይ ያለውም እንስሳ የእኔ ነውና። ❒️ ➥️ |
| | መዝ 104:18 ረጃጅሙ ተራራ የዋልያ መኖሪያ፣ የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው። ❒️ ➥️ |
| | ኢዮ 39:9 “ጐሽ ያገለግልህ ዘንድ ይታዘዛልን? በበረትህስ አጠገብ ያድራልን? ❒️ ➥️ |
| | ኢዮ 39:5 “ለሜዳ አህያ ነጻነት የሰጠው ማን ነው? እስራቱንስ ማን ፈታለት? ❒️ ➥️ |
| | ዘፍ 7:14 ከዱር እንስሳት ከየወገኑ፣ ከቤት እንስሳት ከየወገኑ፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጡራን ከየወገናቸው፣ ከወፎችም ከየወገናቸውና ክንፍ ያላቸው ሁሉ አብረዋቸው ገቡ። ❒️ ➥️ |
| | መዝ 104:23 ሰውም ወደ ሥራው ይሄዳል፤ እስኪመሽም በተግባሩ ላይ ይሰማራል። ❒️ ➥️ |
| | ኢዮ 39:1 “የበረሃ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋልያ ስታምጥስ ተከታትለህ አይተሃል? ❒️ ➥️ |
| | ዘፍ 6:20 ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቈዩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይመጣሉ። ❒️ ➥️ |
| | ኢዮ 38:39-40 “ለአንበሳዪቱ አድነህ ግዳይ ታመጣለህን? የተራቡ የአንበሳ ግልገሎችንስ ታጠግባለህን? እነርሱ በዋሻ ውስጥ ያደባሉ፤ በደን ውስጥም ይጋደማሉ። ❒️ ➥️ |
| | መዝ 148:10 የዱር አራዊትና የቤት እንስሳት ሁሉ፣ በምድር የሚሳቡ ፍጥረታትና የሚበሩ ወፎችም፣ ❒️ ➥️ |
| | ዘፍ 8:19 እንስሳቱ ሁሉ፣ ወፎችም፣ በምድር የሚንቀሳቀሱ ሁሉ በየወገናቸው ከመርከቧ ወጡ። ❒️ ➥️ |
| | ኢዮ 40:15 “አንተን እንደ ፈጠርሁ፣ የፈጠርሁትን፣ ‘ብሄሞት’[81] ተመልከት፤ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤ ❒️ ➥️ |
| | ኢዮ 39:19 “ለፈረስ ጒልበትን ትሰጠዋለህን? ዐንገቱንስ ጋማ ታለብሰዋለህን? ❒️ ➥️ |