| | ዘፍ 9:3 ሕያውና ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ፤ ለምለሙን ዕፀዋት እንደ ሰጠኋችሁ፣ አሁን ደግሞ ሁሉን ሰጠኋችሁ። |
| | ኢዮ 40:20 ኰረብቶች ምግቡን ያበቅሉለታል፤ አውሬዎችም ሁሉ በዙሪያው ይፈነጫሉ። |
| | መዝ 145:15-16 የሁሉ ዐይን አንተን በተስፋ ይጠብቃል፤ አንተም ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸዋለህ። አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤ የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታረካለህ። |
| | ኢዮ 39:4 ግልገሎቻቸውም ይጠነክራሉ፤ በሜዳም ያድጋሉ፤ ተለይተው ይሄዳሉ፤ ወደ እነርሱም አይመለሱም። |
| | ኢዮ 39:30 ጫጩቶቹ ደም ይጠጣሉ፤ እርሱም በድን ካለበት አይታጣም።” |
| | ኢዮ 40:15 “አንተን እንደ ፈጠርሁ፣ የፈጠርሁትን፣ ‘ብሄሞት’[81] ተመልከት፤ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤ |
| | መዝ 104:14 ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ ለእንስሳት ሣርን፣ ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤ |
| | ኢዮ 38:39-41 “ለአንበሳዪቱ አድነህ ግዳይ ታመጣለህን? የተራቡ የአንበሳ ግልገሎችንስ ታጠግባለህን? እነርሱ በዋሻ ውስጥ ያደባሉ፤ በደን ውስጥም ይጋደማሉ። ልጆቿ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፣ ምግብ አጥተው ሲንከራተቱ፣ ለቍራ መብልን የሚሰጥ ማን ነው? |
| | ኢዮ 39:8 በየተራራው ይሰማራል፤ ሐመልማሉንም ሁሉ ለማግኘት ይወጣል። |
| | መዝ 147:9 ለእንስሳት ምግባቸውን፣ የቍራ ጫጩቶችም ሲንጫጩ የሚበሉትን ይሰጣቸዋል። |