| ሰቆ 3:38 ከልዑል አፍ ክፉና መልካም ነገር አይወጣምን? |
| 1ኛ ጢሞ 4:4 እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፥ ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት የሚጣል ምንም የለም፤ |
| መዝ 19:1-2 ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል። ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች። |
| ዘፍ 2:2 እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። |
| ዘጸ 20:11 እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም። |
| ዘፍ 1:8 እግዚአብሔር ጠፈርን ሰማይ ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሁለተኛ ቀን። |
| መዝ 104:31 የእግዚአብሔር ክብር ለዘላለም ይሁን፤ እግዚአብሔር በሥራው ደስ ይለዋል። |
| ዘፍ 1:13 ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሦስተኛ ቀን። |
| ዘፍ 1:19 ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አራተኛ ቀን። |
| ዘፍ 1:23 ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አምስተኛ ቀን። |
| መዝ 104:24 አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፤ ሁሉን በጥበብ አደረግህ፥ ምድርም ከፍጥረትህ ተሞላች። |
| ዘፍ 1:5 እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን። |