Chap.   
እግዚአብሔር የጽድቅ ፀሓይ
☐ 1. ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያውጃሉ።
☐ 2. ቀን ለሌላው ቀን ይናገራል፤ ሌሊትም ለሌሊት ዕውቀትን ይገልጣል፤
☐ 3. ንግግር የለም፤ ቃል የለም፤ ድምፃቸው በጆሮ የሚሰማ አይደለም።[28]
[28] ወይም የሚናገሩት የላቸውም፤ ቃላት የለም፤ ከእርሱ ምንም ድምፅ አይሰማም☐ 4. ያም ሆኖ ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፣ ቃላቸውም[29] እስከ ዓለም ዳርቻ ይወጣል። እርሱ በሰማያት ለፀሓይ ድንኳን ተክሎአል፤
[29] ሰብዓ ሊቃናት የሩምና ሱርስት እንዲሁ ሲሆኑ ዕብራይስጡ ግን ድንበራቸው ይላል።☐ 5. ፀሓይም ከእልፍኙ እንደሚወጣ ሙሽራ ይወጣል፤ ወደ ግቡም እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል።
☑ 6. መውጫው ከሰማያት ዳርቻ ነው፤ ዑደቱም እስከ ሌላኛው ዳርቻ ነው፤ ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም።
  ኢዮ 22:14  በሰማይ ክበብ ላይ ሲራመድ፣ እንዳያየን ጥቅጥቅ ያለ ደመና ይሸፍነዋል።’ ❒️ ➥️
  ቆላ 1:23  ይህም የሚሆነው በእምነታችሁ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በመቆም ከሰማችሁት የወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ ጸንታችሁ ብትኖሩ ነው። እናንተ የሰማችሁትና ከሰማይ በታች ላለ ፍጥረት ሁሉ የተሰበከውም ወንጌል ይኸው ነው፤ እኔም ጳውሎስ ለዚህ ወንጌል አገልጋይ ሆንሁ። ❒️ ➥️
  መዝ 139:9  በንጋት ክንፍ ተነሥቼ ብበር፣ እስከ ባሕሩ ዳርቻ መጨረሻ ብሄድ፣ ❒️ ➥️
  መክ 1:5  ፀሓይ ትወጣለች፤ ትጠልቃለችም፤ ወደምትወጣበትም ለመመለስ ትጣደፋለች። ❒️ ➥️
  ኢዮ 25:3  ሰራዊቱ ሊቈጠር ይችላልን? ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው? ❒️ ➥️
  መዝ 113:3  ከፀሓይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን። ❒️ ➥️
☐ 7. የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስንም መልሶ ያለመልማል፤ የእግዚአብሔር ሥርዐት የታመነ ነው፤ አላዋቂውን ጥበበኛ ያደርጋል።
☐ 8. የእግዚአብሔር ሕግጋት ትክክል ናቸው፤ ልብን ደስ ያሰኛሉ። የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ ዐይንን ያበራል።
☐ 9. እግዚአብሔርን መፍራት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። የእግዚአብሔር ፍርድ የታመነ፣ ሁለንተናውም ጻድቅ ነው፤
☐ 10. ከወርቅ ይልቅ የከበረ፣ እጅግ ከጠራ ወርቅም የተሻለ ነው፤ ከማር ይልቅ ይጣፍጣል፤ ከማር ወለላም ይበልጥ ይጥማል።
☐ 11. ደግሞም አገልጋይህ በእርሱ ጥንቃቄ ያደርጋል፤ እርሱንም መጠበቅ ወሮታ አለው።
☐ 12. ስሕተቱን ማን ሊያስተውል ይችላል? ከተሰወረ በደል አንጻኝ።
☐ 13. ባሪያህን ከድፍረት ኀጢአት ጠብቅ፤ እንዳይሠለጥንብኝም ርዳኝ፤ ያን ጊዜ ያለ እንከን እሆናለሁ፤ ከታላቅ በደልም እነጻለሁ።
☐ 14. መጠጊያዬና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣ በፊትህ ያማረ ይሁን።
 
  
  Chap.