Bible Verses by Topic

ተአምራት በብሉይ ኪዳን

2ኛ ነገሥት 1:9-12
ንጉሡም የአምሳ አለቃውን ከአምሳ ሰዎች ጋር ሰደደ፥ ወደ እርሱም ወጣ፤ እነሆም፥ በተራራ ራስ ላይ ተቀምጦ ነበር። እርሱም። የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ንጉሡ። ውረድ ይልሃል አለው። ኤልያስም መልሶ የአምሳ አለቃውን። እኔስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፥ አንተንም፥ አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ አለው። እሳትም ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳውን ሰዎቹን በላች። ደግሞም ሌላ የአምሳ አለቃ ከአምሳ ሰዎች ጋር ላከበት፤ እርሱም። የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ንጉሡ። ፈጥነህ ውረድ ይላል ብሎ ተናገረ። ኤልያስም። እኔስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፥ አንተንም አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ አለው። የእግዚአብሔርም እሳት ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳውን ሰዎቹን በላች።
30
Pause     Prev     Next