Bible Verses by Topic

ተአምራት በአዲስ ኪዳን

ሉቃስ 14:1-6
በሰንበትም ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት እንጀራ ሊበላ በገባ ጊዜ እነርሱ ይጠባበቁት ነበር። እነሆም፥ ሆዱ የተነፋ ሰው በፊቱ ነበረ። ኢየሱስም መልሶ። በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? ብሎ ለሕግ አዋቂዎችና ለፈሪሳውያን ተናገረ። እነርሱ ግን ዝም አሉ። ይዞም ፈወሰውና አሰናበተው። ከእናንተ አህያው ወይስ በሬው በጕድጓድ ቢወድቅ በሰንበት ወዲያው የማያወጣው ማን ነው? አላቸው። ስለዚህ ነገርም ሊመልሱለት አልተቻላቸውም።
30
Pause     Prev     Next