Online Mezmur  Your Online Mezmur Lyrics 

 

Psa 147:7: Sing to the LORD with thanksgiving; Sing praises on the harp to our God,

Show Version Name:      Bible Cross Reference        Who We Are In Christ        Bible Verses by Topic        

Who we are in Christ (በክርስቶስ ያለን ማንነት)


 ዮሐንስ 15:16  እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።
 ዮሐንስ 15:5  እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።
 ዮሐንስ 3:16  በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
 ዮሐንስ 3:3  ኢየሱስም መልሶ። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።
 ሉቃስ 1:37  ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።
 ፊልጵስዩስ 1:6  በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና፤
 ፊልጵስዩስ 3:20  እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤
 መዝሙር 139:1  አቤቱ፥ መረመርኸኝ፥ አወቅኸኝም።
 መዝሙር 139:14  ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።
 Go Back